ቅዳሴ
ቅዳሴ ማለት “ቀደሰ፣ ባረከ፣ አመሰገነ፣ አከበረ፣ ማለት ሲሆን የቃሉም ትርጉም መቀደስ- መባረክ ማመስገን ማለት ነው _ ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን በአንድ ትንፋሽ አንብበን _ ስንተረጉመው የምስጋና _ መርሐ _ ግብር (የምስጋና ሥርዓት) ማለት ይሆናል።
❖ ሥርዓተ ቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎተ ቍርባን ይባላል፡፡
1.1. የሥርዓተ ቅዳሴ አከፋፈል
በአጠቃላይ ሥርዓተ ቅዳሴ (የጸሎተ ቍርባን ሥርዓት)
በሦስት ይከፈላል-
❖ የመጀመሪያው ክፍል የቅዳሴ ዝግጅት ክፍል ወይም ግብዓተ መንጦላእት፣ ወይም ሥርዓተ ግብጽ ይባላል፡፡ ይህም “ኦ እንየ በዝንቱ ልቡና” ወንድሜ ሆይ በተሰበሰበ ልቡና ጽና(ሁን) ካለው ጀምሮ “ሚ መጠን ዛቲ _ዕለት ግርምት” ይህች ዕለት ምን የምታስፈራ ናት እስከሚለው ያለው ነው፡፡
❖ ሁለተኛ ክፍል የትምህርተ ወንጌል የምክርና የምስጋና ክፍል ሲሆን በተለምዶ ሥርዓተ ቅዳሴ ይባላል። በዚህ የሥርዓተ ቅዳሴ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ከቅዱስ ወንጌል÷ የቅዱሳን የነቢያት ትንቢትና የሐዋርያት _ መልእክታት እንዲሁም የከበረ የጌታ ቅዱስ ወንጌል ይነበባል የተረጎማል፡፡
❖ ሦስተኛ ክፍል ኅብስቱ ወደ ሥጋ አምላክ ወይኑ ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበት፤ የጸሎትና የምስጋና ክፍለጊዜ ነው፡፡ በተለይም በዚህ የጸሎት ክፍለ ጊዜ ከምስጋና ሁሉ የተመረጠ ልዩ ምስጋና “ኀበነ ንህበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ” የባህርይ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስን ሰደህ፤ ይህን ሕብስት ይህን ወይን ለውጠህ፤ ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ትኩስ ሥጋህን ትኩስ ደምህን አድርገህ፤ ከአንተ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ አንድ
መሆንን ስጠን፤ ብሎ ከህኑ ሲያመሰግን ርዕደተ መንፈስ ቅዱስ (የመንፈስ ቅዱስ መውረድ) ይሆናል፡፡ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋ አምላክ ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል፡፡ በጥቅሉ ይኸው የጸሎተ ቅዳሴ ክፍለ ጊዜ ፍሬ ቅዳሴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ የጸሎት ክፍል የሚተገበርበት እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓ ት አሥራ አራት ቅዳሴያ አሉን እነርሱም:
- ቅዳሴ ዘሐዋርያት
- ቅዳሴ እግዚእ
- ቅዳሴ ማርያም
- ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ ፫.
- ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
- ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
- ቅዳሴ ባስልዮስ
- ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
- ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
- ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
- ቅዳሴ ዘቄርሎስ
- ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
- ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
14(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
1.2 ሥርዓተ ቅዳሴን ማን ጀመረው?
❖ ሥርዓተ ቅዳሴን (ሥርዓተ ጸሎተ ቁርባንን) የመሠረተው (የጀመረው) ሊቀካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሙስ ማታ በብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በበዓለ ፋሲካው ማዕድ ተቀምጦ÷ በግዐ ፋሲካውን · ከተመገቡ በኋላ÷ ለደቀ መዛሙርቱ ስለእናንተና ስለብዙዎች ቤዛ የሚፈተትና የሚሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው እንኩ ብሎ ቅዱስ ሥጋውን፧ እንዲሁም ጽዋውን አንስቶ አመስግኖ አክብሮ “ስለእናንተ ስለዓለሙ ሁሉ የሚፈሰው አዲስ ሥርዓት ሆኖ የሚሰጠው ደሜ ይህ ነው፤ ብሎ ክቡር ደሙን በለጋስነቱ – ሰጥቷቸው፤ እንዲህም _ አድርጉ ብሎ _ ሥርዓተ _ ቅዳሴውን መሠረተ፡፡ ሥርዓቱንም በተግባርና በትምህርት አስተማራቸው፡፡ ጸሎተ ቍርባንን አከናወነ (ማI:.26 ቁ26-28፣ ማር.14 ቁ 17-25፣ Λ.Φ.22 14-38: Ph.6 56-59 1.11 23-26)
❖ ይህም የቅዳሴውም ሥርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነው
የመጀመሪያው የዘመነ ወንጌል ቤተ መቅደስ በነበረው ዓልአዛር በተባለው ደገኛ ሰው ቤት ነበር።
❖ ዛሬ የምንቀድሰውን የሥርዓተ ቅዳሴ ቅደም ተከተሉን ያሰባሰበው ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ነው::
1 .3 የመጀመሪያዎቹ አስቀዳሾች እና ቆራቢዎች
የዚህ ጸሎተ ቅዳሴ (ሥርዓተ ጸሎተ ቁርባን) የመጀመሪያ ዎቹ አስቀዳሾችና ቆራቢዎች የነበሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ነበሩ፡፡ ጌታ የጸሎተ ቍርባኑ ሰዓት ባደረሰ ጊዜ ጸሎተ ቅዳሴውን ለማ ከናወን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ፡፡ (ሉቃ.22 ቁ14)
ደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቅዳሴውን አስቀድሰው ቅዳስ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ ለቅዱስ ሥጋህናግ ለክቡር ደምህ ስላበቃኸን ክብር ምስጋና ይግባህ ብለው አመሰገኑ፤ ካመሰገኑ ከዘመሩ በኋላ ወደ
ደብረ ዘይት ወጡ፡፡ (ማቴ26 ቁ30)
በዛሬዋም ቅድስት ቤተክርስቲያን ለጸሎተ ቅዳሴ የእምንሰበሰበው ከዚሁ ተነሥተን ስለሆነ በጸሎተ ቁርባኑ እናመሰግነዋለን ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን ለመብላትና ለመጠጣት በቸርነትህ ስላበቃኸን ብለንም እናከብረዋለን፤ እናገነዋለን፡፡
ስለዚህም ነው ለሥጋወደሙ የበቁና የተዘጋጁ ቅዱስ ቁርባኑን በሚቀ በሎት ሰዓት “እስመ ኃያል ኣንተ እኩት ወስቡህ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም” ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን ቆርሰህ ገምሰህ የዘለዓለም ሕይወትን እናገኝ ዘንድ እንኩ ብሉ ጠጡ ብለህ በለጋስነት የሰጠኸን አንተ ኃያል ነህና ገናና ነህና ክቡር መባል ምስጉን መባል ይገባሃል እያልን የምንዘምረው፡፡ ይህም ዝማሬ ያንጊዜ ሐዋርያት ቅዱስ ቁርባኑን ከተቀበሉ በኋላ እንደ ዘመሩት ያለ ዝማሬ ነው፡፡
1.4 የሥርዓቱ ዋና ዓላማ
የመሥዋዕተ ኦሪት ምግብና መፈጸሙን መጠናቀቁን በምትኩ የሐዲስ ኪዳን የዘለዓለም ሥርዓት የወንጌል መሥዋዕት የሆነውን ከእመቤታችን የነሣውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ቆርሶና ገምሶ በቸርነቱና በለጋስነቱ ለሚያምኑበት እና እንዲሁም የዘለዓለምን ሕይወትን ለሚናፍቁ ሁሉ እንካችሁ ብሉ ጠጡ ብሎ ከመ ስጠት ጋር ለአበው ሐዋርያት _ ለተከታዮቻቸው ሥርዓቱን ለማስ ተማርና ለመፈጸም ነው፡፡ (1ቆሮ.1 ቁ25-26)
እንዲህ ብሎ “ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ሥጋዬንም የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው” (h.6 51-59)::
ክብር ምስጋና ይግባውና የዘለዓለም ሕይ ወት የሚገኝበትን የጸሎተ ቍርባን ሥርዓት ለመሳተፍ (ቅዳሴ ለማስቀደስ) ወደ ቤተክርስቲያን በሄድን ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ እንደ አንዱ ደቀ መዝሙር (እንደ አንዱ ሐዋርያ) ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመረጠንና እንደጠራን ሳንዘነጋ “በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ” (1ኛ ጢሞ.3 ቁ.15) ብሎ ሐዋርያው ለልጁ ጢሞቶዎስ እንደመከረው እኛ ም እንደሚከተለው የሥርዓተ ቅዳሴውን ሥርዓት አውቀን፤ በቤተ እግዚአብሔር እንዴት መኖር እንዳለብን እንማማራለን፡፡ ያለ ሥር ዓት የሚሄዱትን ገሰጿቸው ብሎናልና (2ኛ ተሰሎ.5 ቁ 14)፡፡የሚደረግ ዝግጅት
ብርሃነ ዓለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሁሉም ነገር በአ ግባቡና በሥርዓቱ ይሁን” 1ኛ ቆሮ.14:40 ብሎ እንደመከረን÷ ሥርዓ ትን መማ ርና በሥርዓት መመራት ተገቢ ነው፡፡
ስለሆነም ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በተለይ በዕለተ ሰንበት÷ በዓበይት በአላት÷ በቅዱሳን ክብረ በዓላት
❖ ቅዳሴ ለማስቀደስ
❖ ቁርባን ለመቁረብ
❖ ከጸሎተ ቅዳሴው በረከትን ለማግኘት ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስንመጣ፦ የሚከተለውን ማድረግ ይጠበቅብናል::
ሀ. የሕሊና ዝግጅት ማድረግ
ወደ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ በጎ ሕሊና እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ (የሐ.ሥ.23 ቁ1) (ሮሜ13 ቁ5) አምላካችን እግዚአ ብሔር ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ይለናልና (ምሳሌ. 23 ቁ 26)
ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ከመምጣ ታችን አስቀድሞ በሰንበት ዋዜማ (የልቡና) ዝግጅትን ማድረግ ጸሎተ ቅዳሴውን ለመከታተል ይረዳል፡፡
ይህንን ስንል ስድስቱን ዕለታት በሥራ የባከነውን ልቡናችንን ሰብሰብ አድርጎ ማሳረፍና ወደ ቤተመቅደስ እንዴት መግባት አለብኝ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ በጥንቃቄ ሆነን መግባት አለብን፡፡
በጥንቃቄ መግባት እንዳለብን “ወደ ቤተ እግዚአብሔር በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ» ብሎ የጥበብ ሰው ሰሎሞን ነግሮናልና። (መክ.5 ቁ1)
አሳባችንን ለመሰብሰብ እና ለበጎ ሥራ እንድንዘጋጅ ከሚረዱን ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፦ ሐዋርያው “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብን ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” (2ኛጢሞ.3 ቁ.12-16)፡ ብሎ እንደመከረን፡
❖ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፡፡ (ሮሜ.15 ቁ4-5)
ለ የሰውነታችንን ንጽሕና መጠበቅ-
ተፈጥሮአዊ አካላችን ጥሩ ጠረን እንዲኖረው ሰውነታችን በሰንበት ዋዜማ በመታጠብ መዘጋጀት የራሳችንን ንጽሕና ከመጠ በቅ አልፎ እግዚአብሔር ንጹሐ ባህርይ ስለሆነ ወደሱ በአክብሮት በመቅረብ ባደረግነው ዝግጅት ዋጋ እናገኝበታለን፡፡ ከፈጣሪያቸው ጋር ለመገናኘት የሹትን ቤተ እሥራኤልን ሙሴም እንዲህ ብሎ እንዲዘጋጁ አዘዛቸው፡“ሰውነታቸውን አነጹ ሕዝቡም ልብሳቸውን አጠቡ˚ (ዘጸአት 19፡15)
ሐ. መንፈሳዊ አለባበስ ሥርዓትን መጠበቅ-
የሰውነታችንን ንጽሕና ከመጠበቅ ጋር የአለባበስ ሥርዓትን መጠበቅ ይገባል፡ቅዳስ ያዕቆብ የቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳል ወደ ምትሆን ወደ ቤቴል መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ትዕዛዝ በደረሰው ጊዜ ቤተሰቡን “ንጹሕ ሁኑ ልብሳችሁንም ለውጡ” ብሎ አዟቸ ዋልና፡፡ (ዘፍ.35 ቁ2) ስለዚህ “ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ* አባትህን ጠይቀው እርሱ ይነግርሃል፤ (ዘዳ.32 ቁ.7) እንዳለው ሊቀነቢያት ሙሴ ለመንፈሳዊ ስልጣኔ መሰረቶች የሆኑትን የአበውን የአለባበስ ሥርዓት ጠይቆ አውቆ _ እነርሱን ምሳሌ በማድረግ ለቤተ እግዚአብሔር የሚለበስ የተለየ የቤተክርስቲያን ልብስ ቢኖረን ይመረጣል፤ የተለየ የሰንበት ልብስ ባይኖረን ያን ያለንን አጥበን አጽድተን ለብሰን ብንሄድ መልካም ነው፡፡ በተጨማሪ በተለይ በዕለተ ሰንበት በአጋጣሚ ምክንያት ካልሆነ
በቀር ጃኬት ብቻ÷ ሸሚዝ ብቻ ለብሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እጅግም አያስመሰግን፡፡ ምክን ያቱም ወደ ምድራዊ ሠርግ ቤት ተጠርተን ስንሄድ እንኳ ሙሽራ ውንና ሚዜዎቹን ለመምሰል ተራ ልብስ ለብሰን እንደማንሄድ የታወቀ ነው፡፡ ተራ ልብስ ለብሰን ብንሄድ እንኳ ከበሬታ አናገ ኝም ምክንያቱም አክብሮ የጠራንን ቤተሰቡን አልመበልንምና። (ማቴ.22 ቁ12)
እንደዚሁም ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ደግሞ መንፈሳዊ ተድላ ደስታ የምንቋደስበት፣ ነውርና ነቀፋ የሌለበት የመርዓዊ ንጉሥ ክርስቶስ ንጽሕት የሠርግ ቤት ስለሆነች አባቶችና ወንድ ሞች ኩታቸውን፣ ጋቢያቸውን ደረብ አድርገው፣ መስቀለኛ አጣፍ ተው አደግድገው እናቶችና እኅቶችም እንደዚሁ ባህላዊ ልብሳቸውን ለብሰው፣ ከፈጣሪያቸው ፊት በሰማያውያን መላእክት አምሳል ለምስጋና ቢቆሙ፣ ለእግዚአብሔርም ክብር ነው፡፡ ለአስቀዳሾችም ሞገስ ነው፡፡
መ. ወርኀዊ ልማደ አንስት በተከሠተ ጊዜ መታቀብ
እናቶችና እኅቶች ወርኃዊ ልማደ አንስት በተከሠተ ጊዜ
ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት ራስን ለቁርባን መብቃትና ለቅዳሴ እንዲሁም ሥርዓተ አምልኮ ለመፈጸም እራስን ማዘጋጀት አግባብ አይደለም፡፡ ፍትሐ ነገ አን. 14፡5631፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያንን ንጽሕና ለመጠበቅ ሲባል ነው፡፡
እንደሚታወቀው ቤተክርስቲያን ንጹሕ የአምልኮ ሥፈራ ስለሆነች ከቆ ምንበት ስፍራ ጀምሮ መሬቱን ስመን ተሳልመን ለፈጣሪያችን ያለንን ፍቅር ከመግለጽ ጋር ፍጹም በረከትን እናገኛ ለን ብለን እናምንበታለን፡ስለሆነም አንድ አንድ ጊዜ ይህ ወርሃዊ ክስተት አንድ አንድ እናቶች እህቶች ላይ ከሚጠበቀው በላይ እየሆነ ለመቆጣጠር ስለሚቸገሩ ከዚህ የተነሳ የሌላውን ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ስሜቱን ለማክበር አና በስነ ልቦናው ጉዳት እንዳ ይደርስበት ሲባል ነው እንጂ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ወርኀዊ ልማድ እንደ መርገም ተቆጥሮ አይደለም፡፡
እንዲህ ብሎ ማሰብ በራሱ ኃጢአትም ነው፤ ክህደትም ነው፡፡ እንዲህ ብሎ የሚያስብ ቢኖር እንኳ ቅዱስ ኤፍሬም “ዲያብሎስ ያሳታት ሔዋንን ነጻ አደረጋት” _ ሔዋንን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ነጻ ካደረጋት ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን፤ ለምኝልን አእምሮውን ጥበቡን ሳይብን፤ አሳድሪብን፤ ብሎ እመቤታችንንም ባላመሰገናት ነበር፡፡ በዚህም ምስጋናው ሔዋን የስሕተት ምክንያት ስለሆነች ፈጽሞ አላዳናትም የሚሉ የመናፍቃንን በር ዘግቶባቸዋል።
የሰኞ ው ማር
1.ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ልንጠነቀቅባቸው ከሚያስፈልጉን ነገሮች
ሀ. መውጣትና መግባትን በተመለከተ
- ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጀመረ በኋላ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባት ወይም ከቤተክርስቲያን ውስጥ ወጥቶ መሄድ አይፈቀድም፡፡ ነገር ግን ጸሎተ ቍርባኑ¸ እስኪፈጸም ድረስ የማይቆይ ከሆነ አስቀድሞ ራስን መለየት ይገባል። (ፍት. መን.አን 12፡478)
እንዲህም ሲባል ግን በከባድ ችግር እና ትዕግስት በሚያሳጣ ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከሆነ እንደችግሩ በቀስታ ሆኖ ሌላውን አስቀዳሽ በማይረብሽ ሁኔታ ራስን ማግለል ይቻላል፡፡
- ጸሎተ ቅዳሴው ከተጀመረ በኋላ ዲያቆኑ እትዉ በሰላም እሾህ ሳይወጋችሁ እንቅፋት ሳይመታችሁ በሰላም ወደቤታችሁ ሂዱ ብሎ ሳያሰናብት ወጥቶ መሄድ አይገባም፡፡ (ፍት. መን.አን. 12: N. 92)
ለ. ምራቅን ጺቅ ማለት አግባብ አለመሆኑ
በሥርዓተ ቅዳሴው ውስጥ ሳለን ምራቅን ጺቅ ማለት ክልክል ነው፡፡ (ፍት.መን.አን. 12፡. 476)
ሐ. ስለ ግል ጸሎት
በቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎተ ቍርባኑ ከተጀመረ በኋላ መጽሐፍ ዘርግቶም ሆነ በቃል በንባብ የግል ጸሎትን ማድረስ ክልክል ነው፡፡ ይኸውም ከሚጸለየው ጸሎት ከሚሠዋው መሥዋዕት ይልቅ የኔ ጸሎት ይሻላለ ብሎ ማስብ ነው፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው
ካለ በጠራራ የፀሐይ ብርሃን ሻማ አብርቶ የወጣ ሰውን ይመስላል። ነገር ግን ከአበው በተወረሰው የጸሎት ልምድ አንጻር ቀደም ብሎ ተጀምሮ ያልተፈጸመ ጸሎት ካለ ድርገት ከወረደ በኋላ ቆራቢ ዎች እየቆረቡ ሳለ በጸጥታ ድምፅ ሳያሰሙ መጸለይ ይቻላል። ይህ ሥርዋጽ ነው ሥርዋጽ ማለት የጠመመ ማቅኛ የጎደለ መሙያ የመምህራን አስተያየት ማለት ነው፡፡
መ. ዋዛ ፈዛዛ አይገባም
ክፉ ንግግር የክፉ ሰዎች መለያቸው ነው፡፡ ክፉ ሰው ክፉ ነገርን ከሚያስብበት ልቡናው ክፉ ነገርን አውጥቶ ይናገራል ብሏልና ጌታ (ማቲ.12 ቁ.35) ይህን ክፉ ጠባይ ለማረም እንደ ክቡር ዳዊት ወማዕጾ ዘዐቅም ለከናፍርየ “አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አነ-ር“ (አርምሞን) (መዝ.140 ቁ.3) እያሉ መለመን ተገቢ ነው::
በተለይ በጸሎተ ቅዳሴው ሥርዓት ላይ ሳሉ ዋዛ ፈዛዘ መናገር፣ መሳቅ ክልክል ነው፡፡ የሳቀ ቢኖር ካህን ከሆነ አንድ ሱባዔ (ሰባት ቀን) በቀኖና በጾም በጸሎት በሰጊድ ይቀጣል፡፡ ምዕመን ከሆነ ግን ወዲያው ከሥርዓተ ቅዳሴው ተለይቶ ይውጣ፤ በዕለቱ ሥጋ ወደሙን አይቀበል። (ፍት. መን.አን.12፡ድስቅ.12፣ ኒቅያ 61፣ በስ.72) በሥርዓተ ቅዳሴው ሳለን ከእግረ መስቀሉ መቆማችንን ዘንግ ተን አልባሌ ነገር ብንናገር በዕለተ ዓርብ ከጌታ መስቀል አጠገብ ለመቆም እድሉ ገጥሞት ነገር ግን ኃጢአቱና በደሉ እየታወሰው ምሕረትን በመለመን ፈንታ ያፌዝ የነበረውን በግራ በኩል የተሰቀ ለውን ወንበዴውን እና ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሳደቡ የነበሩትን ቤተ አይሁድን እንዳያስመስለን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ (ማቴ.26 *.39-49)
“ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል” እንዲሉ አበው ሰው ሁሉ ከአነጋገሩ የተነሣ ይከብራል፤ » ከአነጋገሩም የተነሣ ይፈረድበታ ልና፡፡ (ማቴ. 12 ቁ.37)
ሠ. ቂም በቀልን ይዞ ማስቀደስ አይገባም
ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት የለም እንዲሉ አበው በምሳሌያዊ _ አነጋገራቸው መሃሪና ይቅር ባይነትን ገንዘብ ሳያደርጉ ምሕረትንና ይቅርታን ለመጠየቅ ማሰብ ስንፍና ነው፡
ጌታም ክብር ምስጋና ይግባውና እንዲህ ብሎ መክሮናል፡፡ “እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህ ከወንድምህ ታረቅ በኋላም መጥ ተህ መባህን አቅርብ˚ (ማቴ.5 ቁ24) የቂመኛ ሰው ጸሎት ከእሾህ መካከል እንደወደቀ አዝመራ ነው፡፡ ከእሾህ መካከል የወደቀ አዝመራ ከታችም አይዳብር ከላይም አያፈራ:: ከታችም ሳይዳብር ከላይ ቢያፈራ እሾሁን ተጠግተው ፍሬውን አእዋፍ እንዲለቅሙ ቂመኛም ቂሙን ሳይተው ቢጸልይ ቂሙን ተጠግቶ ዲያብሎስ የምስጋውን ፍሬ ለቅሞ ያስቀርበታልና፡፡ /ሕንፃ መነሶሳት/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር