በክርስትና ጥምቀት አንዲት ናት ። (ኤፌ 4:5)
ስለ ህፃናት ጥምቀት ፤
ጥምቀትን ስንቀበል መሠረታችን የክርስቲያን ልጆች ከሆነ በህፃንነታችን ወራት ማድረግ ይገባል ። ስለምን ቢሉ
1. ህፃናት በትምህርታቸውና በአካሄዳቸው ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ እንዲመሩ ለማድረግ ነው ።
2. እነ ኤርምያስ እነ ዮሐንስ መጥምቅ እና ቅዱስ ጳውሎስ ገና በእናታቸው ማህጸን ሳሉ በመንፈስ ቅዱስ ስለተመረጡ ነው ። (ኤር 1:5 ፤ ሉቃ 1:44 ፤ ገላ 1:15)
3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህፃናትን ተዋቸው ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ብሎ እጁን በራሳቸው ላይ አድርጎ ሲባርካቸውና ሲጸልይላቸው ስለነበር ። (ማቴ 19:13-14)

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቃል መሠረት በማድረግ ቀን ለይታ ወንድ ልጅ በአርባ ቀን ሴት ልጅ በሰማንያ ቀን እንዲጠመቁ ወስናለች **። ይኸንኑም ያደረገችበት ምክንያት ኦሪት ለወንጌል ሕግ መቅድም እንደሆነች ሥር ዓቷና ሕጓ ከኦሪትና ከወንጌል የተያያዘ እንዲሆን ስትል በኦሪት ሕግ ወንድ ልጅ ቢወለድ በአርባ ቀኑ ዕጉለ ርግብ ዘውገ ማዕነቅ ይዘው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ያገቡት እንደነበር ። ሴት ልጅም ስትወለድ እንዲሁ በሰማንያ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ያገቡዋት ስለነበር ይህን ትእዛዝ ለመፈጸም ስትል ወሰነች ። ሁለተኛም በኩፋሌ መጀመሪያ እንደተጻፈው አባታችን አዳም በተፈጠረ በአርባ ቀን ወደ ገነት እንደገባ ሔዋንም በተፈጠረች በሰማንያ ቀን ወደ ገነት እንደገባች ስለሚናገር የኛይቱ ቤተ ክርስቲያንም የብሉይ ኪዳንን ሕግ ተመርኩዛ የወንጌልን ሥር ዓት ለመፈጸም ስትል ወንድ ልጅ በአርባ ሴት ልጅ በሰማንያ ቀን እንዲጠመቁ አዘዘች ። (ዘሌ 12:1-5)
ወንድሞቼ ሆይ ዮሐንስ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ። ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው እንደ አለ ትውልዳችንና ነገዳችን ሁሉ ከሥጋዊ ልደት በኋላ ዳግም ከመንፈስ ቅዱስ ተወልዶ የእግዚአብሔር ማደሪያ እንዲሆን በኃይሉ ይርዳን ። አሜን ።
ምንጭ መጽሔተ አሚን
** ልናውቃቸው የሚገቡ ተያያዥነት ያላቸው ነጥቦች :-
1. የህጻኑ ጤንነት የሚያሰጋ ከሆነ ከዚህ ቀን በፊትም ሊፈጸም ይችላል። በችግርና በሌላ ምክንያት ከተጠቀሰው ቀን ቢዘገይ ቤ/ክ የመጡትን ወደኋላ አትመልስም ታጠምቃለች።
2. ሊያጠምቁ የሚገባቸው ሥልጣነ ክህነት ያላቸው ሰዎች ማለትም ቄስ ወይም ጳጳስ መሆን እንዳለባቸው የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል፡፡ ‹‹በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ካህን ነውና ሊያጠምቅ ሥልጣን አለው›› የሚለው አመለካከት የተሳሳተ ነው፡፡ በአጠቃላይ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን መፈጸም የሚገባቸው ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ብቻ እንጂ ሥልጣነ ክህነት የሌላቸው ምእመናን ሊሆኑ አይገባም፡፡ አይሆኑምም፡፡
3. በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተጠመቀ በኋላ ወደ ሌላ እምነት ቢገባ ፥ ኋላም ተጸጽቶ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ቢመለስ ተናዞ (ንስሐ ገብቶ) በማየ ጸሎት (መጽሐፈ ቄደር ተደግሞለት) ይረጫል እንጂ ድጋሚ አይጠመቅም፡፡ ቄደር የንስሐ እጽበት ነው፡፡ ያደፈ ልብስ እንደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢአቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡
4. ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውጭ የነበሩ አማኞች እምነታቸውን ሽረው ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሲመጡ ከዚህ ቀደም እንዳልተጠመቁ ስለሚቆጠር ትምህርተ ሃይማኖትን ከተማሩና ንስሐ ከገቡ በኋላ ይጠመቃሉ ፡፡በክርስትና ጥምቀት አንዲት ናት ። (ኤፌ 4:5)

4. ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውጭ የነበሩ አማኞች እምነታቸውን ሽረው ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሲመጡ ከዚህ ቀደም እንዳልተጠመቁ ስለሚቆጠር ትምህርተ ሃይማኖትን ከተማሩና ንስሐ ከገቡ በኋላ ይጠመቃሉ ፡፡