ደ/መ/ ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በርሚንግሃም ዩናይትድ ኪንግደም

D.M.KIDUS AMANUEL ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH BIRMINGHAM. UK

beteamanuel ቤተ አማኑኤል

ቅዳሴ

ቅዳሴ ማለት “ቀደሰ፣ ባረከ፣ አመሰገነ፣ አከበረ፣ ማለት ሲሆን የቃሉም ትርጉም መቀደስ- መባረክ ማመስገን ማለት ነው _ ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን በአንድ ትንፋሽ አንብበን _ ስንተረጉመው የምስጋና _ መርሐ _ ግብር (የምስጋና ሥርዓት) ማለት ይሆናል።

❖ ሥርዓተ ቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎተ ቍርባን ይባላል፡፡

❖ ሥርዓተ ቅዳሴ ሥርዓተ ጸሎተ ቍርባን ይባላል፡፡

1.1. የሥርዓተ ቅዳሴ አከፋፈል

በአጠቃላይ ሥርዓተ ቅዳሴ (የጸሎተ ቍርባን ሥርዓት)

በሦስት ይከፈላል-

 

❖ የመጀመሪያው ክፍል የቅዳሴ ዝግጅት ክፍል ወይም ግብዓተ መንጦላእት፣ ወይም ሥርዓተ ግብጽ ይባላል፡፡ ይህም “ኦ እንየ በዝንቱ ልቡና” ወንድሜ ሆይ በተሰበሰበ ልቡና ጽና(ሁን) ካለው ጀምሮ “ሚ መጠን ዛቲ _ዕለት ግርምት” ይህች ዕለት ምን የምታስፈራ ናት እስከሚለው ያለው ነው፡፡

❖ ሁለተኛ ክፍል የትምህርተ ወንጌል የምክርና የምስጋና ክፍል ሲሆን በተለምዶ ሥርዓተ ቅዳሴ ይባላል። በዚህ የሥርዓተ ቅዳሴ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ከቅዱስ ወንጌል÷ የቅዱሳን የነቢያት ትንቢትና የሐዋርያት _ መልእክታት እንዲሁም የከበረ የጌታ ቅዱስ ወንጌል ይነበባል የተረጎማል፡፡

❖ ሦስተኛ ክፍል ኅብስቱ ወደ ሥጋ አምላክ ወይኑ ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበት፤ የጸሎትና የምስጋና ክፍለጊዜ ነው፡፡ በተለይም በዚህ የጸሎት ክፍለ ጊዜ ከምስጋና ሁሉ የተመረጠ ልዩ ምስጋና “ኀበነ ንህበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ” የባህርይ ሕይወትህ መንፈስ ቅዱስን ሰደህ፤ ይህን ሕብስት ይህን ወይን ለውጠህ፤ ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ትኩስ ሥጋህን ትኩስ ደምህን አድርገህ፤ ከአንተ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ አንድ

የካህናት አገልግሎት፣ ኃላፊነትና ተግባር

የካህናት አገልግሎት፣ ኃላፊነትና ተግባር

 

የካህናት ኃላፊነትና ተግባር ቀድሞ መጻህፍተ ህግጋት ሳይጻፉ በብሉይ ሆነ በሐዲስ ኪዳን ከዘመነ አበው ጀምሮ እንደየዘመኑ አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ ሰፊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

 

በመሠረቱ ክህነት፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ፣

  • በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ማገልገል፣
  • የአምልኮ ሥርዓት መፈጸምና ማስፈጸም፣
  • ሕዝብን መጠበቅና መምራት፣
  • ስለ ራስ፣ ስለ ሕዝብና ስለ ሀገር ጸሎትና መሥዋዕት ማቅረብ፣
  • ሕዝብን መጠብቅና መምራት፣

የካህናት ሓላፊነትና ተግባር በአዲስ ኪዳን

የካህናተ ሐዲስ ሥልጣን እንደ ካህናተ ኦሪት በዘር የሚወረስ፣ በይገባኛል የሚገኝ መብት ሳይሆን አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከማይሰፈር ብዕሉ ለሰው ልጅ በሰጠው ጸጋ መሰረት ጥሪውን ተቀብለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰለፉ ሰዎች የተሰጠና የሚሰጥ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናውቃለን እናምናለን፡፡ ሢመተ ክህነት ከሊቀ ካህናት ከኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋና ሰማያዊ በረከት በመሆኑ፣ ድኅነተ ነፍስን ማስገኘት ካልተቻለው ከካህናተ ኦሪት የተለየ፣ ለካህናተ ኦሪት ያልተሰጠ ኃይልና ሥልጣን የተገኘበት ሰማያዊ ሐብት ነው፡፡

ካህን፣ ጠባቂ፣ መምህር፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የሕዝብ መሪ አስተማሪ ኖላዊ መንፈሳዊ አባት ሆኖ የዓለምን ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመጥራት የተሰለፈ የእግዚአብሔር ሕግ አስፈጻሚ በመሆኑ ሓላፊነቱ ነፍስን የመጠበቅ ሓላፊነት ብቻ አይሆንም፣ በደዌ ሥጋ የሚፈርሰውን የእግዚአብሔርን ሕንፃ መጠበቅም ሓላፊነቱ ነው፡፡

 

የእውነተኛ ዕረኛ መመዘኛ ነጥቦች

የክህነት አገልግሎት ሰማያዊና ምድራዊ መግቦት ከሆነ ለዚህ ከባድ ኃላፊነት ብቁ ሆኖ ቸር ጠባቂና ታማኝ የክርስቶስ አምባሳደር እኔ ነኝ ብሎ በልበ ሙሉነት የሚቀርቡ ሰው እሱ ማነው ቢባል ሁኔታው ከባድ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ቅ/ጳውሎስ በዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመሰለፍ መመኘት ከሁሉ የበለጠ መልካሙን ሥራ መመኘት መሆኑን ስለ አንቀጸ ካህናት በጻፈው መልእክቱ፣ ‹‹እሙን ነገር ዘይፈቅድ ይሠየም ጳጳስ ሠናየ ግብረ ፈተወ፡፡›› ካለ በኋላ ለክህነት አገልግሎት የሚሰለፍ ሰው፡-

 

  1. ዘአያደሉ ለገጽ፡፡ በፍርድ በብያኔ፣ በጸሎት፣ አይቶ የማያዳላ፡፡
  2. ዘኢያፈቅር ንዋየ፡፡ ኃላፊውን ነብት የማይወድ፣
  3. መፍቀሬ ነገድ ወዘሠናይ ምግባሩ፣
  4. ዘአንጽሐ ርዕሰ ጻድቅ ወኄር፣
  5. ዘምሁር ቃለ ሃይማኖት መምህር ወመገሥጽ በትምህርተ ሕይወት ወይዘልፎሙ ለእለ ይተዋስኡ በማለት መመዘኛዎቹን አስቀምጦአቸዋል፡፡ 1ኛ ጦሞ፡3፡1-7፡፡ ቲቶ 1፡5-9፡

ወጣቱን ትውልድ በኃይማኖት እና በሥነምግባር ማሳደግ

ከ5-7 ዓመት ቅዱስ ቂርቆስ ክፍል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በውጭ ሀገሮች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጆች የምትሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።ይህ አገልግሎት በተለይ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለየ መልክ እና እጅግ ወሳኝ የሆነ ገፅታ አለው። ከሀገሩ በርቀት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መሪ ብቻ ሳትሆን የባህል፣ማንነት እና ስነልቦናዊ ፋይዳ ሁሉ የሚገለጥባት ልዩ አካሉ ነች። ስለሆነም ወጣቱን ትውልድ ወደ መልካም የኑሮ ደረጃ ለማድረስ ከተፈለገ ከሁሉ አስቀድሞ የማንበብ እና የመጻፍ ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ከወላጅ ቤተሰብ የሚጠበቅ ቢሆንም ወጣቱን ትውልድ በተጨማሪ በእውቀት የታገዘ እና መልካም ስነ ምግባርን የተከተለ አስተዳደጋቸውን የሚከታተሉ የእምነት ተቋማት ማደራጀት እና ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው።

በደብራችን ከ20 አመታት በላይ በሀገረ እንግሊዝ ተወልደው እያደጉ ያሉትን ልጆቻችንን የትምህርት እና የስልጠና ዕድልን ለመስጠት አመቺ ጊዜያትና ቦታዎች ያለመኖር ችግሮቻችን ዋነኛ እንቅፋቶቻችን ነበሩ። ነገር ግን በተለይዩ አጋጣሚዎች ትውልዱን በኃይማኖትና በሥነ ምግባር ለማነፅ አቅም በፈቀደ ሁሉ ሰፊ ጥረቶች ተደርጓል። በበርሚንግሃም ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከተቋቋመት ጊዜያት ጀምሮ በተለያየ አቅምና ጊዜ በፈቀደው ሁሉ ስራዎችን ለመስራት ተሞክሯል።
በአሁን ጊዜ በደብራችን እድሜያቸው ከ5 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊ ልጆቻችን ብዛታቸው ከ300 በላይ ሲሆን ይህን የነገው ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ትውልድ በኃይማኖትና በሥነ ምግባር ለማስተማር ሰፊ ስራዎችን እየሰራን ነው። ደብራችን እ.አ.አ. 2023 በገዛው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በከተማው ለሚገኘው ምዕመን መንፈሳዊ አገልግሎትን ከመስጠት በተጨማሪ ትውልድን በኃይማኖትና በሥነ ምግባር የማነፅ ስራዎችን በከፍተኛ ውጪና ለዚህ ዓላማ በተደራጀ “የተተኪ ትውልድ ትምህርት አስተባባሪ ኮሚቴ” እየተሰራ ይገኛል።

ከ10 ዓመት በላይ ቅዱስ ያሬድ ክፍል

ከ8 – 9 ዓመት ቅድሥት አርሴማ ክፍል

ይህን ትውልድ በሥርዓተ ሃይማኖት ማስተማር ለነገው ቤተ ክርስቲያንን ተረካቢ ከማድረግ ባሻገር ለወደፊት የኑሮና ማህበራዊ ሁኔታዎች የሚሰጠው ጥቅም ለሀገሪቱም ለህብረተሰቡ ትልቅ ዋጋ አለው። ወጣቱን ትውልድ ካለአላስፈላጊ ምግባር ተቆጥቦ የወደፊት ኑሮውን ለመምራት ያስችለው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያን ከወላጅ የሚጠበቅ ትልቅ ሥራም ነው።
በሥርዓተ ኃይማኖታችን መሰረት ህፃናት በ 40 እና በ80 ቀናቸው ተጠምቀው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፀጋን ተቀብለው የቤተ ክርስቲያን ልጅነት ካገኙበት ዕለት ጀምሮ ከዚህ ሥርዓተ እምነት እንዳይርቁና እንዳይጠፉ ቅድሚያ የወላጅ ጥበቃ ዋነኛ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ታዳጊ ትውልድ ሥርዓተ ኃይማኖትን ለማስተማር ቦታንና ጊዜን ማመቻቸው የትምህርት አቅርቦቶችን ከቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅ ድርሻ ነው። ስለሆነም ከጥቅምት 2016 ዓ፡ም (Oct 2023) ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 – 18 ያሉትን ታዳጊ ልጆችና ወጣቶች በደብራችን የመማር የማስተማር ሂደት ተጀምሯል። በዚህም በሥርዓተ ኃይማኖትና ሥነ ምግባር የመማር ማስተማር ሂደት ላይ አመርቂ ውጤት ይመጣል ብለን እናምናለን።

የደብሩ ሰንበት ት/ቤት

የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን

ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቱን ትውልድ በአምልኮተ እግዚአብሔርን አፅንቶ በሃይማኖትና በምግባር ከማኖርም ባሻገር ለቤተ ክርስቲያን ቀናኢ የሆኑ አገልጋዮችን አፍርቷል፤ በማፍራት ላይም ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤት በዕለተ ሰንበትና አበይት በዓላት ወቅት ያሬዳዊ መዝሙራትን ከማቅረብም በላይ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትን፣ ቆሞሳትን፣ ጳጳሳትን፣ መምህራነ ወንጌልን፣ ሰባኪያንን እና በልዩ ልዩ አገልግሎት ላይ የሚፋጠኑ ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን ለቤተ ክርስቲያናችን አበርክቷል። ይህ አገልግሎት እንዳይቋረጥና ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ ሁሉ ከነሙሉ ክብሯ ትተላለፍ ዘንድ በያለንበት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤትን ማጠናከር የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል።

የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ታዳጊ ወጣት መዘምራን

በተለይ በዚህ በውጭው ዓለም ልጆቻችንን የምዕራቡ ባህልና እምነትየለሽ ዘመናዊነት እንዳያጠቃቸው በሰንበት ትምህርት ቤት አስመዝግበን ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ እንዲያውቋት ማድረግና በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ ማስቻል የወላጅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆን አለበት። ምክንያቱም ልጆቻችን ኦርቶዶክሳዊት እምነትን፣ ዶግማን፣ ሥርዓት እና ትውፊትን በሰንበት ት/ቤት ካልተማሩ ሃይማኖታችንን ጠብቀውና አስጠብቀው ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አይቻላቸውም፡፡

Beteamanuel Children
የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ታዳጊ ልጆች መዘምራን

በአጠቃላይ ሰንበት ትምህርት ቤት ትውልድን ለመቅረጽ የሚሰጠው ጠቀሜታ ታላቅ ስለሆነ ወጣቶችና ሕፃናት በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን መደበኛ ትምህርት መከታተል እንዲችሉ ማድረግና በማነኛውም ጊዜና ቦታ አርያና ምሳሌ ሁነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት አፅንተው ይይዙ ዘንድ ከሁልጊዜውም በተለየ መልኩ የሁላችንም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መረዳትና በመተግበርም እግዚአብሔር አምላክ የሰጠንን ሃይማኖታዊ ተልእኮ መፈጸም ይጠበቅብናል።

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር

መልአከ ሰላም ቀሲስ አዲስ

ዋና አስተዳዳሪ

መልአከ ሰላም ቀሲስ ሞላ

ም/ሰብሳቢ

መጋቤ ሐዲስ ቀሲስ ዳንኤል

ስብከተ ወንጌል ሃላፊ

አቶ ያሬድ ዘመንፈስ

ዋና ጸሐፊ

አቶ መንገሻ አስገዶም

ንብረት ክፍል

ወ/ሮ ኤደን ኃይሉ

ገንዘብ ያዥ

አቶ ቴዎድሮስ አለፈ

ልማት ክፍል

አቶ ታደለ ሻወል

ሂሳብ ሹም